Imagine dining in a European capital where you do not know the local language. The waiter speaks little English, but by hook or by crook you manage to order something on the menu that you recognise, eat and pay for. Now picture instead that, after a hike goes wrong, you emerge, starving, in an Amazonian village. The people there have no idea what to make of you. You mime chewing sounds, which they mistake for your primitive tongue. When you raise your hands to signify surrender, they think you are launching an attack.
Communicating without a shared context is hard. For example, radioactive sites must be left undisturbed for tens of thousands of years; yet, given that the English of just 1,000 years ago is now unintelligible to most of its modern speakers, agencies have struggled to create warnings to accompany nuclear waste. Committees responsible for doing so have come up with everything from towering concrete spikes, to Edvard Munch’s “The Scream”, to plants genetically modified to turn an alarming blue. None is guaranteed to be future-proof.
Some of the same people who worked on these waste-site messages have also been part of an even bigger challenge: communicating with extraterrestrial life. This is the subject of “Extraterrestrial Languages”, a new book by Daniel Oberhaus, a journalist at Wired.
Nothing is known about how extraterrestrials might take in information. A pair of plaques sent in the early 1970s with Pioneer 10 and 11, two spacecraft, show nude human beings and a rough map to find Earth—rudimentary stuff, but even that assumes aliens can see. Since such craft have no more than an infinitesimal chance of being found, radio broadcasts from Earth, travelling at the speed of light, are more likely to make contact. But just as a terrestrial radio must be tuned to the right frequency, so must the interstellar kind. How would aliens happen upon the correct one? The Pioneer plaque gives a hint in the form of a basic diagram of a hydrogen atom, the magnetic polarity of which flips at regular intervals, with a frequency of 1,420MHz. Since hydrogen is the most abundant element in the universe, the hope is that this sketch might act as a sort of telephone number. | ቋንቋውን በማታውቀው የአውሮፓ መዲና ውስጥ እየተመገብኩ ነው ብለህ አስብ፡፡ አስተናጋጁ የተወሰነ እንግሊዘኛ ብቻ ይናገራል፤ ሆኖም እንደምንም ተጣጥረህ ከምግብ ዝርዝሩ ላይ የምታውቀውን ምግብ በልተህ ከፈልክ፡፡ አሁን ደግሞ እንዲህ ብለህ አስብ፤ የእግር ሽርሽር እያደረክ እያለ ጠፍተህ፣ከዛም ተርበህ እራስህን በአማዞናውያን መንደር ውሰጥ አገኘኸው፡፡ ምግብ የማኘክ ድምጽ እያወጣህ ነበርና መንደርተኞቹ እያሰፈራራሃቸው መሰላቸው፡፡ ሰዎችን አይተህ አጅ ለመስጠት እጅህን ስታነሳ ደግሞ ልታጠቃቸው እንደሆነ አሰቡ፡፡ የጋራ ባልሆነ አውድ ውሰጥ መግባባት አዳጋች ነው፡፡ ለምሳሌ፤ ራዲዮአክቲቭ ንጥረነገር የተከማቸባቸው ቦታዎች ሳይነኩ ለአስር ሺህ አመታት መተው አለባቸው፡፡ በሌላ በኩል የዛሬ አንድ ሺህ አመት የነበረ የእንግሊዘኛ ቋንቋ አሁን ላይ ለአብዛኛው ተናጋሪ ለመረዳት አስቸጋሪ መሆኑ ድርጅቶች ከኑክሊየር ሀይል ዝቃጭ ጋር በተያያዘ ለመጭው ትውልድ ማስጠንቀቂያ ለማስቀመጥ እየተቸገሩ ነው፡፡ ይህን ስራ ለመስራት የተቋቋሙ የስራ ቡድኖች የእሾህ ማማ ከመስራት አስከ የኤድዋርድ ሙንች ጩኸት የተሰኘ ስራ እና ልውጠተዘር ተካሄዶባቸው የማስጠንቀቂያ ሰማያዊ ቀለም የሚሰጡ እጽዋት እስከመፍጠር ድረስ ያልሞከሩት ነገር የለም፡፡ ማናቸውም ግን ለወደፊቱ ጠቃሚ መሆናቸው ማስተማመኛ አልተገኘም፡፡ በዚህ ጽዳጅ የማስወገድ ስራ ላይ ሲሳተፉ ከነበሩ ሰዎች መካከል ይበልጥ ውስብስብ በሆነ ሌላ ግዳጅ ውስጥ ተሰማርተው ነበር፡፡ ይህም ከምድር ውጭ ከሆኑ ባዕዳን ፍጡራን ጋር መግባባት ነው፡፡ ይህ የባእዳን ቋንቋ የሚለው የዋየርድ ጋዜጠኛ፣ ዳንኤል ኦብራኸስ መጽሀፍ ጭብጥ ነው፡፡ ባዕዳን አካላት መረጃ እንዴት እንደሚቀበሉ የሚታውቅ ነገር የለም፡፡ በ1970 ዎቹ መጀመርያ እርቃናቸውን የሆኑ ሰዎችን እና መሬትን የሚያመላክት ካርታ የሚያሳዩ ሁለት ለመገንዘብ ቀላል የሆኑ ምስሎች ፓዮኒር 10 እና 11 በተባሉ መንኮራኩሮች ባእዳን ፍጡራን ሊያዩዋቸው ይችላሉ በሚል ግምት ወደ ህዋ ተልከው ነበር፡፡ እነዚህ መንኮራኩሮች የመታየት እድላቸው እጅግ አናሳ ቢሆንም በብርሃን ፍጥነት የሚጓዝ የራዲዮ ሞገድ ግንኙነት የመፍጠር እድል ይኖረዋል፡፡ ሆኖም መሬት ላይ ያለ የሬድዮ ግንኙነት በተገቢ ፍሪኩወንሲ መቃኘት እንዳለበት ሁሉ፣ ከምድር ውጭ የሚዘረጋ የራድዮ ግንኙነትም እንደዛው መደረግ አለበት፡፡ በፓዮኒር የተላኩት ምስሎች በተመሳሳይ የጊዜ ኡደት የሚዘወሩ መግነጢሳዊ የሀይል ጫፎች ያለው የሀይድሮጅን አተም ንድፍ መሰረት ያደረገ መልእክት በ1420 ሜጋ ኸርዝ ፍርኩዌንሲ ይሰጣሉ፡፡ ይህም ሀይድሮጅን በብዛት የሚገኝ ቁስ ስለሆነ፣ የተላከው ንድፍ እንደ ስልክ ቁጥር ሊያገለግል ይችላል የሚል ተስፋ ስለተጣለበት ነው፡፡ |